የኮቪድ-19 ቫይረስ ምርመራ በ30 ደቂቃ እንደሚደርስ ይውቃሉ?

August 26, 2021
ኮቪድ-19 ምርመራ ባደረጉ በ30 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚያደርስ የኮቪድ-19 መመርመሬያ መሳሪያ (Antigen RDT) በሁሉም መንግስት የጤና ተቋማት ይገኛል፡፡
ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ምልክት ያለው እንዲሁም የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የሚፈልግ የማህበረሰብ ክፍል በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራውን ማግኝት ይችላል፡፡
ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ጥቅሞች(Antigen RDT):_
◾️ምርመራው በተደረገ በ30 ደቂቃ መድረሱ
◾️የኮቪድ-19 ቫይረስ ከተገኝባቸው እራስን በፍጥነት መለየት ስለሚቻል የቫይረሱ ስርጭት መቀነስ ይቻላል
◾️ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ወደ ጤና ተቋም የሚሄድ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ይችላል ውጤቱንም እዛው ይገኛል
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የኮቪድ-19 ምልክት የሚያሳይ፣ የጉንፍን ምልክት ያለበት በአጠቃላይ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የሚፈልግ የማህበረሰብ ክፍል በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት በመሄድ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ እና የኮቪድ-19 ስርጭት የከፋ አደጋ እንዳያደርስ ለቫይረሱ ስርጭት ምክንያት እንዳይሆኑ ኢንስቲትዩቱ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ (Antigen RDT) ምርመራ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
#COVID19Ethiopia
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ