የጤና መረጃን ለማጠናከር ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
የኢንስቲትዩቱ የስረዓተ-ጤናና ስነ-ተዋልዶ ምርምር ዳይሬክቶሬት (Health System and Reproductive Health Research Directorate) ከጤና ሚኒስቴር (Ministry of Healthe)፣ከለንደን እስኩል ኦፍ ሃይጂን ኤንድ ትሮፒካል ሜዲሲን (LSHTM) ጋር በመተባበር ከታህሳስ 8 እስከ 10/2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በአዱላላ ሪዞርት ለጤና ባለሙያዎች መረጃን የማጠናከር የአቅም ግንባታ የስራ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የእናቶች አጠቃላይ የጤና ሁኒታ፣ የጨቅላ ህጻናት ሞት፣ ክትባት ፣ የሣንባ ነቀርሳ፣ የወባ በሽታ፣ እና የህጻናት የምግብ ሁኔታ በተመለከተ በክልሎችና በወረዳዎች በጤና ባለሙያዎች የተሰበሰቡትን መረጃዎች የመተንተንና ትረጓሜ የመስጠት ስነ-ዘዴን ለጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ አውደ ጥናት ነው፡፡
ተከታታይነት ያለው እና እስከ ሁለት ዓመት የሚቆየውን ስልጠና እየወሰዱ ያሉት የጤና ባለሙያዎች በክልልና በአገር አቀፍ ደረጃ የጨቅላ ህጻናት ሞትና የአመጋገብ ስርዓት፣ የእናቶችን ጤና፣ ክትባት፣ ወባን እና የሣንባ ነቀርሳ ላይ ያሉ መረጃዎችን በማሰብስብ ከተለያዩ የጥናት መረጃዎች ጋር በማወዳደር፣ በማነጻጸር ልዩነታቸውንና አንድነታቸውን ገምግመው አና ተንትነው ባቀረቡት መሰረት የመረጃ ጥራት ችግር መኖሩን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በመሆኑም የጤና ባለሙያዎቹ ከዚህ በፊት ያገኙትን ስልጠና መሰረት በማድረግ የመረጃ ጥራት ችግር የተከሰተው በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ በክልልና በሃገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡ ወረዳዎች በጤና ኬላዎች፣ በጤና ማዕከሎች፣ በሆስፒታሎች፣ በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚገኙ ከጤና ባለሙያዎች እና ከተለያዩ መዝገቦች የመጀመሪያ መረጃዎችን የሰበሰቡ በመሆኑ የሰበቧቸውን መረጃዎች የሚተነተኑበቸውን ስነ-ዘዴ እና የትርጓሜ አሰጣጥ አስመልክቶ በምን መንገድ መካሄድ እንዳለበት ግንዛቤያቸውን ለማስፋት ከውጭ አገር በመጡ እና ልምድ ባካባቱ ፕሮፌሰሮች ለባለሙያዎቹ ሰፊ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ባለሙያዎቹ ባገኙት ስልጠና መሰረት የሰበሰቧቸውን መረጃዎች ለመተንተን በቡድን የተቀናጁና እቅድ ያዘጋጁ ሲሆን በቀጣይ በመጋቢት ወር በሚደረገው አውደ ጥናት ላይ አጠናቀው እንደሚቀርቡና የሰሯቸውን ስራዎች ከስልጠናው አንጻር ተግባራዊ ለመሆናቸው የሚታይ መሆኑን ከፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች መረዳት ተችሏል፡፡
መረጃውን በመጠናከር ደረጃ 38 የሚሆኑ ባለሙያዎች ከኢንስቲትዩቱ፣ከመድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ እና ከጤና ሚኒስቴር የተመረጡ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡