የጤና ሚኒሰቴር/የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሃገራችን የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶች ላይ የቁጥጥር እና ምላሽ ስራዎችን ፣የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ እና የጤና ምርምር ተግባራቶች ላይ በመስራት ላይ ይገኛል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በአገራችን ብሎም በአለማችን ቁጥር እነድ የአለምአቀፍ የህብረተሰብ ጤና ስጋት የሆነዉም ወደ አገራችን ከመግባቱ በፊት የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምስተባበሪያ ማእከል አቋቁሞ የቅድመዝግጅት ተግባራቶች ወደ አገራችን ከገባ በሃላ ከባለድርሻ አካላት እና አጋር አካላቶች ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ምላሽ እየሰጠ ይገኛል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን በተሌዩ ድጋፎች ማለትም በሰዉ ሃይል፣በግብአት እና በፋናንስ የምላሽ አቅምን ከመገንባት አንታር የአጋር አካላት ሚና ወሳን መሆኑ ይታወቃል፡፡ከነዚህም አጋር አካላት የአሜሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መእከከል በአገራችን የቴና አገልግሎት ከማገዝ አኳያ አንዱ አጋራችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአገራችን ቁጥር አንድ የህብረተሰብ ጤና አደጋ የሆነዉን የኮቪድ 19 ምላሽ ስራዎችን ለማጠናከር የጤና ስርአታችንን መገንባት ላይ ማለትም የበሽታዎች ቅኝት እና አሰሳ ማጠናከር፣ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታን ከማስፋት እና ማጠናከር፣ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ከማስፋት እና ማጎልበት፣የጤና ባለሙያዎችን አቅም ግንባታ ከማጠናከር አኳያ ተኩረት ያደረገ የጤና አገልግሎቶችን ለህብረተቡ ተሰራሽ ከማድረግ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሁን እየሰታቸን የሚገኙ የምላሽ ስራዎችን ከማጠናከር ባዘጋጀዉ የድጋፍ እቅድ ከ የአሜሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መእከል ጋር የ20 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት የጋራ ስምምነት አድርጎ ወደ ትግበራ ለመግባት አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ይህ ትግበራ የኮቪድ-19 ስራዎችን እና ሌሎችን የህበረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ከማሳለት፣እና ከማጠናቀር ለአገራችን ጠና ስርአት አፈታጠም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምላሽ ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት አፈጻጸምን ይመራል፣ ስትራቴጂዊ የስራ አፈጻጸምን ማለትም የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ፣ ቅኘት፣ የሰው ሃይል ማደራጀት፣ የመረጃ ስርዓት እና የላቦራቶሪ ድጋፍ ለኮቪድ 19 ምላሽ ያካሂዳል፡፡ የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል በብሔራዊ እና በክልል ደረጃ የኮቪድ 19 ምላሽ ስራዎች የደገፈ ሲሆን የክትባት ስረጭትም እንዲሳለጥ የበኩሉን አድረጓል፡፡
ከኮቪድ 19 ወረርሽን የተማርነው እንዴት የአንድ ወረርሽኝ ስጋት ምን ያክል ባልተጠበቀ ሁኔታ እና ፍጥነት እንደሚሰራጭ ነው፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መሰረታዊ የሕብረተሰብ ጤና የቅኝት ስራዎች እና ምላሽ አሰጣጥን፣ የሰው ሀይል ለማትን፣ እና ተዛማጅ የላቦራቶሪ እና መረጃ ስርዓትን ለማጠናከር እንደመልካም እድል ይታያል፡፡
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የበሽታ ቅኝትን፣ የላቦራቶሪ ስርዓትን፣ ኢንፍሉዌንዛ መሰል በሽታን ለመከላከል፣ ከባድ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት በሽታን ለመከላከል፣ የአስቸኳይ ጊዜ ስራዎች ማዕከላት መረብን፣ የመስክ ኤፒዲሚዮሎጂ የሥልጠና ፕሮግራምን፣ ተከታታይ ክትባቶችን፣ የኮቪድ 19 ክትባት ስርጭትን እና የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ሂደቶችን ያጠናክራል ይደግፋል፡፡
ያለውን የሕብረተሰብ ጤና መሠረተ ልማት ከኢትዮጵያ የዝግጁነት እና ምላሽ ዕቅድ መሰረት የኮቪድ 19 ን ባለው የጤና ስርዓት ውስጥ መካተትን እና ባልተማከለ መልክ ምላሽ መስጠትን ፕሮጀክቱ አጥብቆ የሚሰራበት ጉዳይ ነው፡፡
ባለፈው ዓመት የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የኢትዮጵያን ለኮቪድ 19 እንድትዘጋጅ እና ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተለያዩ ድጋፎች ሲያደርግ ቆይቷል፣ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
- ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ስልጠናዎች መስጠት
- የድንገተኛ ስራዎች ላይ ቴክኒካዊ ድጋፍ መስጠት፣ የላቦራቶሪ ስራዎች ፣ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ፣ ወደ ሀገር መግቢያ በሮች ላይ የሙቀት ልየታ ስራ፣ የአደጋ ጊዜ ተግባቦት እና የማሕበረሰብ ተሳትፎ እና የበሽታ ቅኝት ላይ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
- ተከታታይ ክትባቶች አገልግሎት እና ስረዓት ማጠናከር እና
- የመስክ ኤፒዲሞሎጂ ስልጠና መስጠት ናቸው፡፡
ይህ ድጋፍ የአሜሪካውን የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከልን ሌሎችን የኢንስቲትጡቱን ተልእኮ ከማስፈጸም ሲያደርግ የነበረውን የረጅም ጊዜ ጥረት እና እርዳታ የሚያዳብር ነው፡፡ የማዕከሉ የኢትዮጵያ የጤና ደህነንትን ለማሻሻል የሚያደርገው ድጋፍ ሀገሪቱን ለሚጠሩ የጤና አደጋዎች ኮሮና ቫይረስን ጨምሮ በብቃት ፈጣን ምላሽ መስጠት ከፍተና ሚና ይጫወታል፡፡