የጾታ ጥቃት የማስቆም ዓመታዊ በዓል በኢንስቲትዩቱ ተከበረ

December 10, 2019
የኢንስቲትዩቱ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት የጾታዊ ጥቃት የማስቆም የነጭ ሪቫን ንቅናቄ ዓመታዊ በዓል ህዳር 30/2012 ዓም በኢንስቲትዩቱ የህጻናት ማቆያ ግቢ ውስጥ የኢንስቲትዩቱ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት ተከበረ፡፡
የጸረ ጾታዊ ጥቃት ዓመታዊ በዓል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ28ኛ፣ በሃገራችን ለ14ኛጊዜ የተከበረ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ደግሞ “ሴቶችን እና ህጻናትን ከጥቃት በመጠበቅ ሁላችንም ሃላፊነታችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል ለ8ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡
ወ/ሮ ኑሪያ ዩሱፍ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የበአሉን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ስለ ጾታዊ ጥቃት ምንነት እና ህጻናትን አስመልክቶ የተለያዩ ትምህርታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የተዘጋጀውን የህጻናት ማቆያ ቦታ በበዓሉ ተሳታፊዎች የተጎበኘ ሲሆን የሕጻናት ማቆያው በመዘጋጀቱ የተለያዩ ምስጋናዎች ከበዓሉ ተሳታፊዎች ከመቅረባቸውም በላይ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ከመድረኩ መሪዎች ተገቢውን መልስ ተሰጥቶበት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡