የፖሊሲ ተደራሽነትን ለማጐልበት ያለመ አዉደ ጥናት በእዉቀት ሽግግርና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ተካሄደ
የኢትዮጰያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእዉቀት ሽግግርና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዘላቂ የልማት ግቦችን ከግብ ለማድረስ የሚቀረፁ ፖሊሲዎች መረጃን እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ፕሮጀክት ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ብሎም ለማዳበር በአዳማ ከተማ ከግንቦት 8- 11/2016 ዓ.ም አውደ ጥናት አካሄደ።
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ወ/ት ፊርማዬ ቦጋለ አውደ ጥናቱ ለባለድርሻ አካላት ፖሊሲ አወጣጥና ዉሳኔ አሰጣጥ በሳይንሳዊ ማስረጃ ማስደገፍን እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ((Leaning together to advance Evidence and Equity in Policymaking to achieve the Sustainable Development Goals (SDGs) ((LEEPS)) የተጀመረዉን ፕሮጀክት ዓላማዎች እና አካሄዶችን ያስተዋወቁ ሲሆን በፖሊሲ ቀረፃ ወቅት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የስነ-ተዋልዶ ጤና እና ሰነ-ጾታ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎችን መለየትን ያለመ ነው።
በአውደ ጥናቱ ላይ የዳይሬክቶሬቱ የፈጣን ምላሽ አገልግሎት (Rapid Response Services) ምንነት እና ሌሎች ተያይዥነት ያላቸው ገለፆዎች በዳይሬክቶሬቱ ተመራማሪዎች የተደረገ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች፣ የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።