የፖሊዮ ቀንን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓም አከበሩ

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የአለም የፖሊዮ ቀንን በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓም አከበሩ።
ኢትዮጵያ የፖሊዮ ቫይረስን ጨርሶ ለማጥፋት የሚደረገዉን ጥረት እውን ለማድረግ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡትን ዋና ዋና ስትራቴጅዎች ማለትም የክትባት ሽፋንን ማሳደግ እና ጠንካራ የቅኝት ስርዓት መገንባት ላለፉት አመታት ስትተገብር የቆየች ሲሆን፤ አመርቂ ውጤቶችንም ማስመዝገብ ችላለች። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና አጋር አጋላት ጋር በመተባበር በክትባት እጥረት የሚመጣ የፖሊዮ ወረርሽን ምላሽ ለመስጠት ባለፈዉ አመት አገር አቀፍ የፖሊዮ ከትባት ዘመቻን ከ17 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ እድሚያቸዉ ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት በሁለት ዙር በጥቅምት እና በሚያዚያ 2014 ዓም በተሳካ ሁኔታ መስጠት ተችሏል። ከዚያም ባለፈ የጸጥታ ችግር በነበረባቸዉ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ እድሚያቸዉ ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ተደራሽ ያደረገ የመጀመሪያ ዙር የክትባት ዘመቻ በመስከረም ወር 2015 ዓም የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛዉን ዙር በመጪው ህዳር ወር 2015 ዓም ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሕበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የአፋር ከልል ጤና ቢሮ እና የአፋር የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የአጋር አካላት ተወካዮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።