የ2013 የሩብ ዓመት አፈጻጸምና ቀጣይ ዕቅዶች ዙሪያ የተዘጋጀው የሦስት ቀን ወርክሾፕ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የሩብ ዓመት አፈጻጸምና የቀጣይ ዘጠኝ ወራት ዕቅዶችን የማስተሳሰርና በላብራቶሪዎች አክሪዲቴሽን ዙሪያ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች የስራ ኃላፊዎች ጋር በቢሾፍቱ ከተማ የ 3 ቀናት ምክክር አካሄደ፡፡
ኢንስቲትዩቱ ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም በመዳሰስ የ2013 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸምና ረቂቅ ስትራቴጂክ ፕላን በዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ያቀረበ ሲሆን በክልሎችም በኩል ደግሞ ያለፉት ወራት አፈጻጸም ሪፖረቶች ላይ ሰፊና ገንቢ የሀሳብ ልውውጥ ተካሂዶአል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ውይይቱን የመሩ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች የየዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ እንዲሰጡበት ተደርጎአል፡፡
ዶ/ር ኤባ አባተ ትኩርት በሚሹና ምላሽ ባልተሰጠባቸው ነጥቦች ላይ በማቶከር በተለይም የዓለም ሁሉ ሥጋት በሆነው የ covid 19 ወረርሽኝ በሀገራችን ላይ የፈጠረውን ተግዳሮተ በአፅንኦት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፡፡የተከሰተው ችግርና ይህንኑ ተከትሎ የተገኘው ትምህርት በቀላሉ የሚገመት እንዳልሆነና በሽታውን ከመከላከል አንጻር በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተው ካደረሰው ጥፋት ጎን ለጎን በርካታ ተሞክሮዎች የተገኙበትና በሀገር አቀፍ ደረጃ አቅም የፈጠርንበት አጋጣሚ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡አያይዘውም ወረርሹኝን ለመከላከል በተደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው የተገነኘውን አቅም አሰባስቦ ለበለጠ ድል ተግቶ መስራት እንደሚገባ በአንክሮ ጠቁመዋል፡፡በተጨማሪም በዓለም ባንክ ዕርዳታ የሚገነባውና ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጭምር አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የላብራቶሪ ግንባታ ለክልሎችም ጭምር ትልቅ አቅም የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑ ግንዛቤ አግኝቶ አሁን ያሉት ላብራቶሪዎች አክሪዶቴሸን የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመፍጠር ከወዲሁ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የቀጣይ ዘጠኝ ወራት ዕቅዶችን የማስተሳሰርና በበጀት ዓመቱ የላብራቶሪ አክሪዲቴሽን ዙሪያ የመከረው የ 3 ቀናት ወርክሾፕ ሲጠናቀቅ ዶ/ር ኤባ ከምንግዜውም በላይ ተግተን በመስራት የተሻላ ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልበትን አቅጣጫ በማመላከት የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡