የ2014 በጀት ዓመት ሁለተኛው የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ፎረም ተጠናቀቀ
March 28, 2022
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሐረር ከተማ ሲያካሂድ የነበረው የ2014 በጀት ዓመት ሁለተኛው የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ፎረም በተሳካ ሁኔታ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና የውይይት ዕቅድ መሰረት የተጠናቀቀ ሲሆን ቀጣዩም ፎረም በደቡብ ምዕራብ ክልል የካሄዳል፡፡
በፎረሙ ላይም የተለያዩ ተያያዥነት ያላቸው ሪፖርቶች የቀረቡ ሲሆን ባለፈው ፎረም ላይ እንዲተገበሩ በእቅድ ተቀምጠው የተፈጸሙ እና ያልተፈጸሙት ከነምክንያታቸው የቀረቡ ሲሆን ለቀጣይም እንዚህን ለመፈጸም ውይይት ተደርጎባቸው አቅጣጫ ተቀምጦባቸዋል፡፡
የፎረሙን ውይይት የመሩት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ በውይይቱ ወቅት ለቀረቡ ሀሳቦች እና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከክልል ጀምሮ እስከ ፌደራል ድረስ በተቀናጀ መልኩ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በዝግጅቱ መጨመረሻ ቀንም የፎረሙ ተሳታፊዎች በሐረር ከተማ የጽዳት ዘመቻ ያደረጉ ሲሆን በጁገል ሆሲፒታል የሚገኘውን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከልን ከጎበኙ በኋላ ቀጣይ ለሚያዘጋጀው ክልል እና ለሌሎች የክልል የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከሎች የማስታወሻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡