ግለለሰሰብን መሰረት ያደረገ የኤች አይቪ ቅኝት አመታዊ የግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ
ግለሰሰብን መሰረት ያደረገ የኤች አይቪ ቅኝት አመታዊ የግምገማ መድረክ ከአዲስ አበባ፣ከአፋር፣ ከአማራ ከቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ከድሬ ዳዋ፣ ከሀረሬ ከሶማሌ፣ ከጋምቤላ ከኦሮሚያ፣ ከሲዳማ፣ ከደቡብ ክልል እንዲሁም የተለያዩ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ። በመድረኩም ከሁሉም ክልሎች የመጡ አካላት ግለለሰብን መሰረት ያደረገ የኤች አይቪ ቅኝት አስመልክቶ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት አቅርበዉ ሰፋ ያለ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።
የጤና ሚኒስቴር አገልግሎትና ፕሮግራም ዘርፍ ም/ድኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በመድረኩ ተገኝተዉ እንደተናገሩት በኤች አይቪ ቅኝት ከጀመሩ ሀገራት ኢትዮጲያ ቀዳሚ ሀገር መሆኗን ጠቅሰዉ ስርጭቱ በተወሰኑ ከተሞች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አሳሳቢ በመሆኑ ያለዉን ክፍተት ማጥበብ እና የመረጃ ጥራት አያያዝ ስራ መጨመሩን ገልጸዋል።
የኢትዮጲያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኤች.አይቪ ኤድስ እና ቲቢ በሽታ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳሮ አብደላ በተደረገው ጥናት የተገኘዉን ዉጤት ያቀረቡ ሲሆን በጾታ በመለየት 62% ከፍተኛ ድርሻ የሚይዙት ሴቶች መሆናቸዉን፣ የቀን ሰራተኞች 38.8% መሆናቸዉን፣ ከ15-19 የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ወጣቶች በቫይረሱ መያዛቸዉን ጥናቱ እንደሚያሳይ ገልፀዋል።
በጤና ሚኒስቴር የአገልግሎትና ፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ጽ/ቤት ሀላፊ እና አማካሪ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ያደታ በማጠቃለያዉ ተገኝተዉ እንደተናገሩት የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር ዋና ትኩረት የተሰጠበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል። አክለዉም በሁሉም አካል ሴቶችና ወጣቶችን መሰረት በማድረግ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙምላሽ ሰጪ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረዉ መሰራት እንዳለባቸዉ ገልፀዋል።
በፕሮግራሙም በድሬዳዋ ከተማ ለይ የሚገንኙትን የመንግስት ሆስፒታሎች ጉብኝት ተደርጎል።