የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ሪፈራል ላቦራቶሪ የተጠናከረ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

የክልሉ ላቦራቶሪ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በርካታ ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን፣ በመንግስት እና በአጋር ድርጅቶች የክልሉ ላቦራቶሪ ህንጻ እንደ አዲስ ተገንብቶ በቅርቡ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፣ አዲሱ የላቦራቶሪ ግንባታ ባለ ሶስት-ወለል ህንጻ የምርቃት ስነ-ሰርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳረደር ክቡር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ኡመር፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የክልሉ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
እንደ-አዲስ ወደ ስራ የገባው የክልሉ ሪፈራል ላቦራቶሪ ባለ-ሁለት ወለል ህንጻ የተለያዩ አገልገሎቶችን እንዲሰጥ ታሰቦ የተገነባ ነው፡፡ በዋናነትም የበሽታ ቅኝት እና የወረርሽኝ ልየታና ምላሽ የመስጠት፣ የሪፈራል እና የሪፈረንስ ምርምራ እና የደጀን ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት(Back-up laboratory services ) የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም በዋናነትም ከዚህ ቀደም ሲሰጥ ከነበረው መደበኛ የላቦራቶሪ ባክአፕ ምርመራ አገልግሎቶች በተጨማሪ የሞሎኪውላር ላቦራቶሪ፣ የማይክሮ ፕውሎጂና ማይኮሎጂ ምርመራ፣ ኢላይዛ እና ሌሎች የሴሮሎጂ ምርመራ፣ የላቦራቶሪ ጥራት ቁጥጥር (Quality Assurance) እና ሌሎች ዲፓርትመንቶች ያካተተ ነው፡፡
በተጨማሪም፣ ላቦራቶሪው በክልሉ ላሉ የሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያ ላቦራቶሪዎች የወባ እና የቲቢ ማይክሮስኮፒ ሪኤጀንቶችን አዘጋጅቶ ያከፋፍላል ይህም ከወጪ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልሉ ጋር በመተባበር ዋና ዋና ላቦራቶሪ መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶችንም በግዥ በማሟላት የላቦራቶሪውን አገልግሎት የበለጠ በዘመናዊ መልኩ እንዲደራጅ አስችሎታል፡፡