ለሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ወጤታማነት የተቀናጀ ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ክንፍ በእቅድ መከታተያ እና መገምገሚያ መተግበሪያ (Monitoring and Evaluation Tool) ከኦፕሬሽን የስራ ክፍሎች ጋር አቅዱን አቀናጅቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በዕቅድ ቅንጅቱ ወቅት እንደተናገሩት ባለፈው ዓመት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የተለያዩ ወረርሽኞች ተከስተው አስፈላጊው የቁጥጥር እና የምላሽ ስራዎች በመሰራታቸው ሁሉኑም እጅግ በተሳካ ሁኔታ መወጣት ተችሏል፣ ለዚህም እስከ በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናዎች ተሰጥተዋል፤ ለዚህ ደግሞ ዋናው በእቅድ በመሰራቱ ነው በማለት የተቀናጀ እቅድ እንዴት ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ነኢማ ዘይኑ የኢንስቲትዩቱ የበሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት፣ የክንፉ እቅድ መጀመሪያ ከሁሉም የክንፉ ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች፣ ከአለም አቀፍ የጤና ህግጋት፣ ከብሔራዊ ዕቅድ እና ከኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ እቅድ ጋር እና አንጻር የተቀናጀ ሲሆን አሁን ደግሞ ከኢንስቲትዩቱ የኦፕሬሽን ክፍሎች ጋር በዚህ የእቅድ መከታተያ እና መገምገሚያ መተግበሪያ እየተቀናጀ ይገኛል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኦፕሬሽን ክፍል ኃላፊዎች እንደገለጹት ከሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ጋር በጋራ ሲሰሩ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ቀደም በማለት በጋራ በመሆን ዕቅድን በጋራ እና በቅንጅት ማቀዱ ለማንኛውም አይነት ስራዎችን በተሳለጠ እና በተሳካሁኔታ መወጣት እንዲቻል እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡