ኢንስቲትዩቱ 11 ከሚሆኑ የሃገሪቱ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መረጃን አስመልክቶ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የኢንስቲትቱ የብሔራዊ የጤና መረጃ ማደራጃ ማዕከል የጤና እና የስነ-ሕዝብ ሰርቪላንስ ሳይት ካላቸው 11 የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አጠቃላይ መረጃን አሰመልክቶ በቀንጅት ለመስራት የሚያሰችል የመግባቢያ ሰነድ የካቲት 18/2020 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ ዋና አላማ በሃገር አቀፍ ደረጃ በጋራ እና በቅንጅት በመተባበር የመረጃና የማስረጃ ፍላጎትን ለማርካት፣መረጃዎች የሚሰበሰቡበትንና የሚተነተኑበትን መንገድ እንዲሁም የመረጃ ቅብብሎሽ በመፍጠር የልምድ ልውውጥ ስራዎችን በማዳበር የሕብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ሚያስችል የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለሕበረተሰቡ ፣ለሚመለከታቸው አካላትና ለአጋሮች ማድረስ የሚስችል የመግባቢያ ሰነድ ነው፡፡
ዶ/ር ኤባ አባተ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በመግባቢያ ሰነዱ የወይይት ፕሮግራም ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዶ/ር አለምነሽ ሃይለማሪያም የብሔራዊ ጤና መረጃ ማደራጃ ማዕከል ኃላፊ ደግሞ መረጃ ማዕከሉ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የሰራቸውን በርካታ እንቅስቃሴዎች በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
አጠቃላይ አረጃዎችን አስመልክቶ ኢንስቲትዩቱና ዩኒቨርሲቲዎች በቅንጅትና በጋራ የመሰራታቸው አላማውና የመጨረሻ ውጤቱ ምንድን ነው፣ ምን ምን ነገሮች ተግባራዊ መደረግ አለባቸው፣ ከዩኒቨርሲቲዎቹና ከኢንስቲትዩቱ የሚጠበቀው ምንድን ነው፣ በቀጣይ በጋራና በቅንጅት በመሰራቱ የሚገኙ አገር አቀፍና አለም አቀፍ እድሎች ምን ይመስላሉ የሚሉትን እና ሌሎችም የጤና መረጃዎች የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዘዳንቶች የመግባቢ ሰነዱ ተፈርሟል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር፣ 11 የዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶችና ምክትል የጤና እና የስነ-ሕዝብ ሰርቪላንስ ሳይት አስተባባሪዎች እንዲሁም የብሔራዊ ጤና መረጃ ማደረጃ ማዕከል ኃላፊ እና ባለሙያዎች በአጠቃላይ ከ50 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች በመግባቢያ ሰነዱ የውይይት ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል፡፡