የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተከሄደ ነው

የኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣የፓራሳቲክ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ከየካቲት 26 እስከ 28/2012 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ በድሬ ሆቴል የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው፡፡
የግምገማው ዋና አላማ በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች በ6 ወራት ውስጥ ከእቅድ አንጻር የተከናውኑ ተግባራትን በመገምገም ክፍተት የታየባቸውን የምርምር ስራዎች የክፍተት ምክንያቶችን በመለየት በቀጣይ የተለያዩ ተግባራትን በማካሄድ የተሻሉ አፈጻጸሞችን ለማስመዝገብ የተዘጋጀ የግምገማ መድረክ ነው፡፡
ዶ/ር ገረመው ጣሰው የኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣የፓራሳቲክ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የግምገማ መድረኩ የመክፈቻ ስነ-ስረዓት ወቅት የ6 ወራት የቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በዳሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ የስራ ቡድኖችና ባለሙያዎች በ2012 ዓ.ም በግምሽ አመቱ የእቅድ አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ግምገማ በማድረግ እና ክፍተቶችን በመለየት እንዲሁም የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ዳሬክቶሬቱ በቀጣይ የተሻሉ አፈጻጸሞችን እንዲያስመዘግብ ተፈልጎ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ የኢንስቲትዩቱ የእቅድ፣ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አጠቃላይ የእቀድ አስተቃቀድና የአፈጻጸም ሪፖርት አደራረግን አስመልክቶ በርካታ ዝርዝሮችን ያቀረበ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣የፓራሳቲክ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት የ6 ወራት አፈጻጸም 80 ፐርሰንት ማስመዝገቡንም
ገልጻል፡፡
መልካም አስተዳደርን፣አጠቃላይ የስራ ስነ-ምግባርን ፣ኦዲትን፣ጸረ ሙስናን፣ ፋይናንስን አስመልክቶ የተለያዩ ባለሙያዎች በጽሁፍ የቀረቡ ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ የምርምር ባለሙያዎች ደግሞ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በጽሁፍ እየቀረቡ ውይይትና ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የመልካም አስተዳደር፣ የኦዲት፣የስነ-ምግባር ፣የሰው ሃብት ፣የእቅድ ግምገማ እና ክትትል ዳይሬክቶሬት ሃላፊዎች እና ተወካዮች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ከ60 በላይ በግምገማ መድረኩ ላይ እየተሳተፍ ይገኛሉ፡፡