ኢንስቲትዩቱ ከሲዲሲ-ኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ሶሳይቲ ፎር ላቦራቶሪ ሜድስን ጋር የሥራ ውይይት አደረገ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዲሲ-ኢትዮጵያ/CDC-Ethiopia እና ከአፍሪካ ሶሳይቲ ፎር ላቦራቶሪ ሜድስን ((African Society for Laboratory Medicine) (ASLM)) ጋር በመተባበር ባለፉት አምስት ዓመታት ASLM ከአሜሪካ-ሲዲሲ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ላቦራቶሪ ዘርፍ ያከናወናቸው እንዲሁም በትግበራ ላይ ባሉ ስራዎች ላይ ግንቦት 1/2016 ዓ.ም የሶስትዮሽ የጋራ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስጀመሩት አቶ ዳንኤል መለሰ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ በንግግራቸውም በዋናነት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከASLM ጋር በመተባበር ባለፉት አምስት ዓመታት ስለተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ አጠቃላይ ስራዎች አንስተው ካብራሩ በኋላ፣ ASLM በአሁኑ ጊዜ በላቦራቶው ዘርፍ እያበረከተ ስላለዉ አጠቃላይ ድጋፍ አመስግነዋል። እዲሁም ASLM ከሲዲሲ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ገዝቶ በስጦታ ያበረከታቸውን የቨዲዎ ኮንፈረንስ እና ሌሎች እቃዎችን ከASLM ፕሮጀክት ማኔጀር ከአቶ አዲሱ ከበደ እና ከሲዲሲ-ኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ዳን ዊልያም እጅ ተቀብለዋል፡፡
ASLM ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር በላቦራቶሪው ዘርፍ ያከናወናቸውን እና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ አቶ አዲሱ ከበደ በፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፡ ከተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ እና አጠቃላይ ገለፃ ሰጥተዋል። በተለይም ASLM የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል በተመረጡ የኤች-አይ-ቪ ሞሎኪውላር (HIV Viral load and Early infant diagnosis) ምርመራ አገልግሎት ለሚሰጡ ላቦራቶሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ዓለም አቀፍ የጥራት እውቅና እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን እና በዚሁም ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ሶስት ላቦራቶሪዎች አለም አለምአቀፍ የጥራት እውቅና ማረጋገጫ እንዲያገኙ ያስቻለ ሲሆን በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመትም በተመሳሳይ አምስት ተጨማሪ ላቦራቶሪዎች የጥራት እዉቅና እንዲያገኙ ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ከHIV Viral load የሞሎኪውላር-ምርመራ ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ቆሸሻ (Waste generated from HIV viral load testing) አወጋገድ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ስልጠና በቅርቡ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ ASLM እያዘጋጀ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን፣ ከስልጠናውም በኋላም ትግበራውን ለማገዝ እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከASLM ጋር ያለውን የጋራ ትብብር እና ቅንጀታዊ አሰራርን በይበልጥ አጠናክሮ በሚቀጥልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡