በወቅታዊ የወባ ወረርሽኝን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት ላይ ውይይት ተካሄደ
![በወቅታዊ የወባ ወረርሽኝን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት ላይ ውይይት ተካሄደ](https://ephi.gov.et/wp-content/uploads/2024/07/Picture1-1024x477.png)
ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በወቅታዊ የወባ ወረርሽኝን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት ላይ ሃምሌ 1/2016 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ውይይት ተካሄደ፡፡
ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በውይይት መድረኩ ወቅት እንደገለጹት የወባ ወርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ከሃሳብ ወጥተን ወደ ተግባር ግብተናል በመሆኑም አሁን የተሻለ ስራና ውጤት እተመዘገበ ነው፡፡ በመሆኑም የክልል አመራሮች ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ከፍተኛ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በመውሰድ እንዲሁም ከኃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመስራት የአንድም ሰው ህይወት በዚህ የወረርሽኝ በሽታ ህይወቱ እንዳያልፍ መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የውይይት መድረኩን በመምራትና አቅጣጫ በመስጠት ያስተባበሩ ሲሆን ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋ ዳዳሬክተር አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተሰራ ያለውን የወባ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራትን ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም በሁሉም ክልል የሚገኙ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች በየክልላቸው የተከናወኑ የመከላከል ስራዎችን፣ የታዩ ክፍተቶችን እና በቀጣይ መቀረፍ የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ወረርሽኞችን በሚገባ በመከላከልና በመቆጣጠሩ ረገድ በታቀደው ልክ ውጤታማ እንዲሆን በወረዳዎች እና በቀበሌዎች የሚታዩ ክፍተቶችን ትኩረት በመስጠት መከታተልና ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ማድረግ እንዲሁም የመረጃ ተአማኒነት እና ፍጥነት ላይ ተገቢውን ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
የቀረቡ ሪፖርቶችን መሰረት በማድረግ ውይይት የተካሄደ ሲሆን አጠቃላይ የታዩ ክፍተቶች በአጭር ጊዜ መስተካከል እንደሚገባቸው፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸውና ወረርሽኙን በመከላከልና በመቆጣጠር በኩል ልዩ ትኩረት በመስጠት ተገቢውን ውጤታ ስራ መሰራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡