A delegation of members of the South Korean parliament paid a working visit to the Ethiopian Public Health Institute (EPHI)
A delegation of members of the South Korean parliament paid a working visit to the Ethiopian Public Health Institute (EPHI).
Dr. Mesay Hailu, Director General of the EPHI, welcomed the fifteen-member delegation at his office. The purpose of the visit is to explore and strengthen ongoing support for health sector projects in Ethiopia funded by the Global Fund and GAVI.
Extensive discussions were made regarding the Institute’s 100-year successful journey, its current public health emergency management activities such as emergency preparedness, public health surveillance and emergency response, public health research, laboratory capacity building, and health data management and analytics activities. The delegation expressed their readiness to provide all the necessary support and enhance the ongoing collaborations.
የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ አባላት ልዑካን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተገኝተው የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡
አስራ አምስት አባላት የያዘውን የልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ሲሆኑ፤ የጉብኝቱ ዓላማ በኢትዮጵያ በግሎባል ፈንድ እና በዓለም አቀፉ የክትባት ህብረት/ትብብር የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወኑ የጤናው ዘርፍ ፕሮጀክቶችን ለመዳሰስና ቀጣይ ድጋፍ ለማጠናከር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የኢንስቲትዩቱን የ100 ዓመታት ስኬታማ ጉዞ፣ በአሁኑ ጊዜ የሚያከናውናቸውን የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል ዝግጁነት ቅኝት እና ምላሽ፣ የሕብረተሰብ ጤና ምርምር፣ የላብራቶሪ አቅም ግንባታ እንዲሁም የጤናና ጤና ነክ መረጃዎች ክምችት አስተዳደር ቅመራና ትንተና ስራዎችን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገ በኋላ የልዑካን ቡድኑ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡