የኢንስቲትዩቱ BPR በአዲስ መልክ እየተጠና መሆኑ ተገለጸ
July 22, 2019
የኢንስቲትዩቱ BPR ወቅቱን ባገናዘበና አሁን ካለው የህብረተሰብ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ሊመጣጠን
በሚያስችል ደረጃ በአዲስ መልኩ በማጥናት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከኢንስቲትዩቱ
የተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ለጥናቱ ከተቋቋሙት አብይ ኮሚቴዎች
ጋር በመሆን በተጠናው ጥናት የመጀመሪያ ረቂቅ ላይ ከሃምሌ 12 እስከ 14/2011 ዓ.ም
በናዝሬት ከተማ በድሬ ሆቴል ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ ወቅት ሁሉም የስራ ክፍሎች ለውይይት መነሻ የሚሆን የየስራ ክፍላቸውን የቡድን
አደረጃጀት መግለጫ፣ዓላማ እና የስራ ዝርዝር ይዘው የቀረቡ ሲሆን በአብይ ኮሚቴው ከቀረበው
ረቂቅ ሰነድ ጋር በማስተያየት በስፋትና በጥልቀት ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ወቅት የተነሱትን ነጥቦች መነሻ በማድረግ አብይ ኮሚቴው ከBPR ባለሙያዎች ጋር በጥልቀት በመገምገምና በመፈተሽ ሁለተኛውንየመወያያ ረቂቅ ሰነድ እንደሚያቀርብ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል::