Delegates from ten member states, Africa CDC, PEPFAR, and US-CDC made a working visit to the Ethiopian Public Health Institute.
Director generals and heads of various departments from the National Public Health Institutes (NPHIs) of ten African Union member states attended the African Public Health Institutes Collaborative (APHIC) Inaugural Meeting and made a working visit to the Ethiopian Public Health Institute (EPHI).
The new APHIC initiative is a joint initiative between Africa CDC, the U.S. President’s Emergency Plan for AIDS Relief (PEPFAR) within the State Department Bureau of Global Health Security and Diplomacy, and the United States Centers for Disease Control and Prevention (U.S.-CDC).
APHIC aims at strengthening leadership within NPHIs, fortifying health systems, and advancing critical public health functions to sustain progress in HIV response across Africa. Through peer-to-peer learning and strategic partnerships, APHIC strives to empower NPHIs and enhance public health outcomes on the continent.
Dr. Mesay Hailu, the director general of EPHI, gave a speech at the inaugural meeting and during the visit and emphasized the Ethiopian government’s commitment to strengthening EPHI. The Director General explained EPHI’s role in leading and executing effective public health emergency management for strong national health security, conducting research, scientific evidence synthesis and generation, building sustainable and resilient laboratory systems for high-quality laboratory services, enhancing digital health data science, analytics, and information systems, and improving core public health capacity development.
The delegates visited the Public Health Emergency Operations Center, Data Management and Analytics Center, HIV Molecular Laboratory, Microbiology Laboratory, and Core-Genomics Sequencing Facility.
Finally, Dr. Mesay reaffirmed the institute’s commitment to enhance essential public health functions, integrate public health components of HIV response, strengthen workforce development, disease surveillance, and laboratory networks, coordinate emergency operations centers, and enhance data management and utilization.
ከአስር የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ ከአፍሪካ ሲዲሲ (Africa CDC)፣ ከፔፕፋር (PEPFAR) እና ከዩኤስ-ሲዲሲ (US-CDC) የተውጣጡ ልዑካን በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አደረጉ።
በአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ትብብር (African Public Health Institutes Collaborative) ምስረታ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ ከአስር የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ብሔራዊ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች የተውጣጡ ዋና ዳይሬክተሮች እና የስራ ክፍል ኃላፊዎች፤ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
አዲሱ የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ትብብር፤ በአፍሪካ CDC ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የኤድስ እርዳታ አስቸኳይ ዕቅድ (PEPFAR) እና በዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (US-CDC) መካከል የጋራ ተነሳሽነት ነው::
የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ትብብር ዓላማው በብሔራዊ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ውስጥ ያለውን አመራር ማጠናከር፣ የጤና ሥርዓቶችን ማጎልበትና በመላው አፍሪካ በኤች አይ ቪ ምላሽ ረገድ እድገት እንዲኖር ወሳኝ የሆኑ የህብረተሰብ ጤና ተግባሮችን መደገፍ ነው። ይህ ትብብር በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች መካከል የመማማሪያ መድረክ እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት በመፍጠር ኢንስቲትዩቶቹን ለማብቃትና በአህጉሩ ላይ የህብረተሰብ ጤናን ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ በስብሰባው እና በጉብኝቱ ወቅት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማጠናከር ያደረገውን ቁርጠኝነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠንካራ ብሄራዊ የጤና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን መምራት፣ ጥራቱን የጠበቀ ዘላቂ የላብራቶሪ አገልግሎት ማቅረብ እና ጠንካራ የላቦራቶሪ ስርዓት መገንባት፣ የህብተረሰብ ጤና ምርምር በማድረግ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለጤና ፓሊሲ ግብዓት ማቅረብ፣ እንዲሁም ዲጂታል የጤና ዳታ ሳይንስን፣ ትንታኔዎችን እና የመረጃ ስርዓቶችን ማሻሻል የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቁልፍ ሚናዋች መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
ልዑካኑ፤ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኙትን ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማእከል፣ የዳታ አስተዳደርና ቅመራ ማዕከል፣ የኤች አይ ቪ ሞለኪውላር ላቦራቶሪ፣ ማይክሮባዮሎጂ ላቦራቶሪ፣ እንዲሁም አዲስ የተከፈተውን የዘረመል ላቦራቶሪ ማዕከላትን ጎብኝተዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር መሳይ፤ ኢንስቲትዩቱ አስፈላጊ የሆኑ የህብረተሰብ ጤና ተግባራትን ለማጎልበት፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ምላሽ ስራዎችን ከህብረተሰብ ጤና ጋር ለማቀናጀት፣ የሰው ሀይል ልማት ለማጎልበት፣ የበሽታዎች ቅኝትና የላብራቶሪ አውታሮችን ለማጠናከር፣ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማእከላትን ለማስተባበር፣ እንዲሁም የመረጃ አያያዝና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።