EPHI’s DDG & Directors Visited THRI
The Ethiopian Public Health Institut’s (EPHI) research wing directorate directors led by the Institute’s Deputy Director General Dr. Getachew Tollera visted Tigray Health Research Institute (THRI) on November 23/2023.
Dr. Masresha Tessema EPHI’s Food Science and Nutrition Research Directorate Director indicated that one of the discussion was to conduct Food and Nutrition Strategy Baseline Survey in Tigray Region which will help the region to design various kinds of nutrition interventions. And the survey is financially supported by BMGF and UNICEF. After THRI’s status was presented Dr. Masresha has presented about EPHI and his Directorate.
EPHI’s Parasitic, Bacterial and Zoonotic Diseases Research Directorate’s Director Dr. Geremew Tassew explained that his Directorate discussed on decentralizing the Rabies laboratory services to the Region’s Health Research Institute and provide it’s services in the region, to conduct joint researches on Malaria, Leishmaniasis, Schistomaisis and other neglected tropical diseases.
Among the delegates Dr. Theodros Getachew who is Director of EPHI’s Health Systems and Reproductive Health Research Directorate and Dr. Gemechu Tadesse Director of HIV/TB Research Directorate also discussed on the status of research surveys that were supposed to be launched but couldn’t done because of the conflict, quality of health facilities quality and service equity, status of HIV, TB and the needed capacity building and resource supports from the directorate will continue respectively.
የኢንስቲትዩቱ ም/ል ዋና ዳይሬክተር እና የምርምር ዳይሬክተሮች የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የተመራው የኢንስቲትዩቱ የምርምር ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች መቀሌ ከተማ የሚገኘውን የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩትን ህዳር 13/2016 ዓ.ም ጎበኙ::
የኢንስቲትዩቱ የምግብ እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ እንደገለጹት የጉብኝቱ አንዱ አላማ በትግራይ ክልል የFood and Nutrition Strategy Baseline Survey ለማስጀ መር ሲሆን ይህ የደሰሳ ጥናት ክልሉ ስነ ምግብን በተመለከተ ለሚያዘጋጃቸው ስትራቴጂዎች ግብአት የሚሆን ሲሆን በBMGF እና UNICEF የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ ይሆናል። በጉብኝቱም ስለ ክልሉ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለፆ ከቀረበ በኋላ ዶ/ር ማስረሻ ስለ ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ስለ ዳይሬክቶሬታቸው በፅሁፍ አቅርበዋል።
ዶ/ር ገረመው ጣሰው የኢንስቲትዩቱ የፕራሲቶሎጂ፣ ባክቴርያል እና እንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርም የእብድ ውሻ በሽታ የላቦራቶሪ ምርመራን ወደ ትግራይ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማምጣት አገልግሎቱን ለክልሉ ሕብረተሰብ ማዳረስ፣ በወባ በሽታ ላይ የጋራ ጥናት ማካሄድ፣ በአፈር የሚተላለፉ በሽታዎች፣ ሺስቶማይስስ እና ሌሎች የተዘነጉ የበረሀ በሽታዎች ላይ ውይይት ታደርጓል።
የኢንስቲትዩቱ የስርአተ ጤና እና ስነ ተዋልዶ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ ጌታቸው እና የኤች አይ.ቪ እና ቲቢ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ገመቹ ታደሰ በበኩላቸው በክልሉ ያሉ የጤና ተቌማት የአገልግሎት ጥራት እና የአገልግሎት ተደራሽነት፣ በተከሰተው የሰላም ችግር ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የተለያዩ የዳስሳ ጥናቶችን በተመለከተ ምክክር የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ስላለው የኤች. አይ.ቪ እና ቲቢ ሁኔታዎችና በቀጣይ ስለሚደረገው የአቅም ግንባታ እና የማቴሪያል ድጋፎችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።