EpiGen ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል
EpiGen በሽታዎችን በዘረመል ደረጃ ለመርመር የላብራቶሪ አቅምን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት መስከረም 7/2016 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።
በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ ዶ/ር መብራቱ መሠቦ እንዳሉት የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ በሽታዎች በአገር ውስጥ እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ በማድረግ እና የመከላከል ስራዎች በመስራት ከተከሰቱም ደግሞ በህብረተሰቡ ላይ ትልቅ ጉዳት ሳያደርሱ በፍጥነት ለማቆም ሳይንሳዊ የሆኑ ዘዴዎች ሲተገብር መቆየቱን ገልጸዋል።
ዶ/ር መብራቱ በሽታዎች አሉ የሉም ብሎ አስቀድሞ በአገር ውስጥ አቅም ለመረዳትና ለማሳወቅ የሚያስችል ሙሉ አቅም እንደአገር እንዳልነበር ጠቁመው በተለይ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ባለፉት ሦስት አመታት ከፍ ያለ የአገር ውስጥ አቅም ለመፍጠር፣ በላብራቶሪ፣ በሠው ሀይል፣ የበሽታዎችን ቅኝትን ከፍ ከማድረግ አንጻር ጤና ሚኒስቴር በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
የዚሁ አካል የሆነው የኢፒ ጂን ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት የአውሮፓ ህብረት፣ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት ጋር በመሆን ትልቅ የጥናት ማእከል የበሽታዎች ቅኝትን ዘመናዊ የሚያደርግ፣ ሳይንቲስቶች ምርምር የሚያደርጉበት፣ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የትምህርት እድል የሚያገኙበት እና ጥናትና ምርምር የሚያደርጉበት፣ የመመርመሪያ መሳሪያዎችም በአገር ውስጥ የማምረት አቅምን የሚጨምር ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ተናግረዋል።
የኢፒ ጂን የተለያዩ በሽታዎች ምንነት እና በሽታዎች በቆይታቸው የሚያመጡትን ለውጥ በጁኖሚክ ሲኩዌንስ በሚባል ቴክኖሎጂ ማለትም በተህዋስያኑ በዘረመል ደረጃ ለመለየትና ለመመርመር የሚያስችል ፕሮጀክት መሆኑንና ለጤና ሚኒስቴር፣ በጤና ዙርያ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጉዳዩን ለማሳወቅ እና ፕሮግራም ለመቅረጽ፣ ለፖሊሲ ዝግጅት ግብአት ለማድረግ ታስቦ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን የገለጹት ዶክተር መብራቱ ሳይንቲስቶቹ የአገር ውስጥ አቅምን ከፍ ለማድረግ የሚረዱ የጥናት ስራዎች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ መልእክት አስተላልፈዋል።
የፕሮጀክቱን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረት ፈንድ የሚደረግ ሆኖ የአውሮፓ አባል ሀገራት የሆኑት የጀርመን ፣ የስፔን እና የኔዘርላንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከአገር ውስጥ ደግሞ የአርማወር ሃንሰን ምርምር ኢኒስቲትዩትና አምስት ዩኒቨርስቲዎች የተካተቱበት ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።
ዶlር ጌታቸው ፕሮጀክቱ አምስት አመት የሚቆይ ሆኖ ከመላው ኢትዮጵያ በተመረጡ ሆስፒታሎች የሚተገበር እና ከሶስት መቶ ሆስፒታሎች መረጃ በመሠብሠብ ችግሮችን በመለየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ አቅጣጫ የሚሰጥበት፣ ከ300 ጤና ተቋማት ባለሞያዎችን የአቅም ግንባታ ስልጠና እንድያገኙ የሚደረግበት ፕሮጀክት መሆኑን አስታውቀዋል።
የማክማስተር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶlር ዳዊት ወልዳይ በበኩላቸው ኢፒጂን ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን ሳይንትስቶች አውሮፓ ካሉ አጋር የጥናት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ፕሮጀክት ግራንት ተጽፎ አሸናፊ በመሆን ወደ አገር ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ የሚያጠነጥነው ተላላፊ በሽታዎች ገና ከመከሰታቸው በፊት ወይም በሽታው በተከሠተ ከ24 ሰአት በፊት በዘረመል በመመራመር መረጃን በአፋጣኝ ለውሳኔ ሰጪ ማለትም ለጤና ሚኒስቴር ለማስተላለፍ እንዲቻል አቅም ለመገንባት ነው ካሉ በኋላ ለበሽታ መከላከል ከፍተኛ ፋይዳ ያለው እንደሆነ ነው