The 9th Public Health Emergency Management (PHEM) Forum Has been Completed
The 9th and the 1st round of the Public Health Emergency Management (PHEM) Forum for the fiscal year which was being held in Afar Region Semera city was completed on January 3, 2024 in the presence of Minister of the Ministry of Health Dr. Liya Tadesse.
Regional Public Health Institutes have presented their reports which focused mainly on responses given to major public health emergency incidents. Active discussions were made on each of the presentations followed by way forwards.
The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) Deputy Director General, Dr. Melkamu Abte indicated that relevant teams from the Ministry of Health; Expanded Programme on Immunization (EPI), Malaria Prevention and Control, Nutrition, and Field Epidemiology and Laboratory Training Programme Coordinators; as well as participants from other sectors like Ministry of Water and Energy, and Ministry of Defense and Federal Police have participated in the forum, realizing the multisectoral approach to Public Health Emergency Management.
Dr. Mesay Hailu, the Director General of EPHI, explained that the Institute is working to further strengthen the health emergency preparedness, disease intelligence, and response system for the efficient and timely response, control and prevention of public health emergencies. Dr Mesay added that the EPHI has created an enabling environment for comprehensive organization and operations for a responsive public health emergency management system including strategies for cross-border diseases prevention and control at all designated points of entry throughout the country. Having such a structure and system in place from National-to- Sub-national levels, will highly support the Research, Data management and analysis, and the Laboratory capacity functions to be able to effectively forecast, detect, prevent, control and respond to public health emergencies.
“Thus, this forum is very important to share experiences from regions and stakeholders to lay out joint plans for a successful public health emergency management,” added Dr. Mesay.
Minister of Health Dr. Liya Tadesse on the closing remark reminded that the public health emergencies in the last three years including COVID-19 were opportunities to strengthen our public health emergency responses. These responses need coordination among the different sectors, and needs to be institutionalized; and in order to realize this, a legal framework is under preparation.
Regarding the PHEM and Emergency Operating Centers (EOCs) in the newly established regions, the Minister stressed that the Ministry will continue its support to organize them, and also expand EOCs to Zonal level depending on the regional context.
የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ጉባዔ ተጠናቀቀ
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከታህሳስ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው 9ነኛው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ጉባዔ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በተገኙበት ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም በስኬት ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ እንደተናገሩት በጉባዔው ላይ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የተለያዩ የስራ ክፍል የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና የቡድን መሪዎች፣ የክልል ጤና ቢሮዎች እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ከፍተኛ ኋላፊዎች እንዲሁም ከጤናው ሴክተር ውጭ ያሉ ባለድርሻ አካላት እንደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስ የጤናው ዘርፍ ተወካዮች መገኘታቸውን በመግለጽ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የጤናው ሴክተር ባለድርሻ እካላት ጋር በጋራ የማቀድ፣ የመስራትና የመተባበር ልምዳችንን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርም በበኩላቸው የድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ጨምሮ ማናቸውንም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን አስቀድሞ የመከላከል፣ ሲከሰቱም ምላሽ የመስጠት እንዲሁም የመልሶ ማገገምና የማይበገር የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ሥርዓትን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አስፈላጊ የሆኑ መዋቅሮች እና አደረጃጀቶችን በመፍጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። እነዚህ መዋቅሮችና አደረጃጀቶች የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር፣ የምርምር፣ የስልጠና፣ የመረጃ ቅመራና ትንተና እንዲሁም የላብራቶሪ አቅም ግንባታ ሥርዓቶችን የሚያካትት ሲሆን አነዚህም አደረጃጀቶች በተዋረድ በክልልሎችም የምናገኛቸው ይሆናል። ኢንስቲትዩቱ ከግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጅ ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮፕያ አየር መንገድ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከበሽታዎች መከላከልና mመቆጣጠር ማዕከል (CDC) እና ሌሎች ባለድርሻ እካላት ጋር በመተባበር ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን እና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ በሽታዎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ከማከናወን በተጨማሪ የወረርሽኞችን ከስተት አስቀድሞ የመተንበይ ስራን እየተገበረ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚይስፈልግ እንስተዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ሃገሪቱ ባለፉት ዓመታት በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት ያለንን የሕብረተስብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ሥርዓት ክፍተቶችን በግልጽ በማሳዬት ለማስተካከልና ለማጠናከር ዕድል የፈጠረ እንደነበር አንስተዋል። በዚህም ከተለያዩ መንግስታዊ ከሆኑ እና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ያለው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የታየበት አንደሆነና ከዚህ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የህግ ማዕቀፍ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በተጨማሪም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከላት በሁሉም ክልሎች የተቋቋሙ ሲሆን እንደ ክልሎቹ ነባራዊ ሁኔታ በዞኖች እና በወረዳዎች ደረጃም ማቋቋም እንደሚያስፈልግና አዲስ ለተመሰረቱ ክልሎች የተለየ ትኩረት በመስጠት ለማደራጀትና ነባሮቹን ለማጠናከር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያደርገውን የሙያ፣ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችንም እንዲሁ ደረጃ በደረጃ በጋራ እየተቀረፉ የሚሄዱ መሆኑን አንስተዋል።