አንድ ጤናን መሠረት ያደረገ የፊልድ ኢፒዲምሎጂ ስልጠናን ያጠናቀቁ ሠልጣኞች ተመረቁ

ከተለያዩ የትግራይ ክልል የተወጣጡ የጤና ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ጤናን (#OneHealth) መሠረት ያደረገውን የፍሮንት ላይን የፊልድ ኢፒዲምሎጂ መሠረታዊ ስልጠናን አጠናቀው ዛሬ የካቲት 25/2017 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በተካሄደው ስነ ስርዓት የዕውቅና ምስክር ወረቀታቸውን ተቀብለዋል።
በዚህ ስልጠና የሰዉና እንስሳት ጤና እንዲሁም የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ወ/ሮ ነኢማ ዜይኑ በኢትዮጰያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ዝግጁነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዚህ የፓይለት የፍሮንትላይን ስልጠና ዘርፈ-ብዙ ባለሙያዎችን በጥምረት በማድረግ የተሰጠ እንደመሆኑ ለአንድ ጤና ተግባራዊነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለዉ እንደመሆኑ ከዚህኛው ዙር በምንወስደው ልምድ ቀጣዮቹ ዙሮች የበለጠ የተሳኩ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
በሌላ በኩልም የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አማኑኤል ኃይሉ በክልሉ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ይህ ስልጠና በመጀመሪያ ዙር ለክልሉ ባለሙያዎች መስጠቱን አመሰግነው አግባብነቱንም በተግባራዊ ተሞክሮዎች አስረድተዋል።
አቶ ህሉፍ ሀጎስ የአከባቢ እና አየር ንብረት ባለሰልጣን ምክትል ሀላፊ እና ዶ/ር ታጠቅ ቦጋለ የAFENET አስተባባሪ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ተመሳሳይ ስልጠናዎች በመካከከኛ እና ከዛም ባሻገር መሰጠት እንደሚገባቸው ከሰልጣኞች የተሰጠውን አስትያየት ሲመልሱ እንዳሉት የዚህ የፓይለት ስልጠና አጠቃላይ አፈፃፀም ለሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ ስልጠናው በተለያዩ ደረጃዎች መስጠት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።