የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ የአትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና አንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች ደስታቸውን ገልጸዋል

September 10, 2025
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለአትዮጵያ ብልጽግና መሰረት ፣ ለህብረተሰብ የተሻለ ጤናም ፋይዳው የጎላ መሆኑም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተዘጋጀው የእንኳን ደሳላችሁ መርሀግብር የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ እንደተናገሩት ታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለመላው አትዮጵያውያን እና ለአትዮጵያ ወዳጆች እጅግ የሚያስደስትና ለመላ ህዝባችን ታሪካዊ ድል መሆኑን ገልጸው ለመበልጸግ የያዝነው ውጥን ስኬታማ እንደሚሆን ማረጋገጫ ነው ብለዋል። የበለጸገና ጤናማ ትውልድ ለማፍራትም የማይተካ ሚና አለው ያሉት ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ለሚያደርገው ጥረትም መልካም እድል ይዞ እንደመጣ አስረድተዋል።
በመርሀግብሩ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ የማኔጅመንት አባላት እና የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምርቃት እንዳስደሰታቸውም ገልጸዋል።
የታላቁን የህዳሴ ግድብ ምርቃት አስመልክቶ የእግር ጉዞ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ የተደረገ ሲሆን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውጣትና የኢትዮጰያ ብሄራዊ የሕዝብ መዝሙርን በመዘመር የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡