ኢንስቲትዩቱ እና የትሮፒካል ሕክምና ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት ያለመ ሳይንሳዊ የምርምር መድረክ ተካሄደ EPHI and Institute of Tropical Medicine Hold Joint Scientific Research Forum

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ከዓለም አቀፉ የትሮፒካል ሕክምና ኢንስቲትዩት (Institute of Tropical Medicine – ITM) እና ከተለያዩ የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ከፍተኛ የሳይንስና የምርምር የምክክር መድረክ በኢንስቲትዩቱ ተካሂዷል።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ ኢንስቲትዩቱ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ከማመንጨት ባለፈ የምርምር ግኝቶችን ወደ ተግባራዊ የጤና አገልግሎትና ፖሊሲ በመቀየር የሕብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዕለቱ መርሐ-ግብር ላይ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የሚስተዋሉ የእናቶችና ሕፃናት ጤና ተግዳሮቶች፣ ተላላፊ በሽታዎች እንዲሁም የከተማ ነዋሪዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ልዩነቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ዶ/ር ጌታቸው በንግግራቸው በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በትሮፒካል ሕክምና ኢንስቲትዩት (ITM) ትብብር ሊካሄድ በታቀደው “የወሊድ ጊዜ የአእምሮ ጤናን ከእናቶች እና ከሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ጋር በኢትዮጵያ ማቀናጀት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው አዲስ የምርምር ፕሮጀክት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው አብራርተዋል። ይህ ጥናት በእርግዝናና ከወሊድ በኋላ የሚከሰቱ የአእምሮ ጤና ችግሮችን ከመደበኛው የእናቶች ጤና አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲና መመሪያዎች ለማጠናከር ያለመ ነው።
በመጨረሻም ኢንስቲትዩቱ የሀገር ውስጥ የምርምር አቅምን የሚያሳድጉና ዘላቂነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ትብብሮችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
EPHI and Institute of Tropical Medicine Hold Joint Scientific Research Forum
————————————-
The Ethiopian Public Health Institute (EPHI), in collaboration with the Institute of Tropical Medicine (ITM) and various development partners, hosted a high-level scientific research and consultative forum at the Institute’s headquarters.
Delivering the opening remarks, EPHI’s Deputy Director General, Dr. Getachew Tollera, emphasized that the Institute goes beyond generating scientific evidence by translating research findings into practical health interventions and policies to improve public health outcomes across Ethiopia.
The forum featured in-depth discussions on pressing public health priorities in low- and middle-income countries, including emerging maternal and child health challenges, infectious diseases, and urban health inequalities.
Dr. Getachew particularly highlighted a proposed joint EPHI–ITM research initiative titled “Perinatal Mental Health into Maternal and Sexual & Reproductive Health Services in Ethiopia.” The study aims to address critical gaps by integrating mental health care during pregnancy and after childbirth into routine maternal and reproductive health services, thereby strengthening national health policies and guidelines.
In closing, Dr. Getachew reaffirmed EPHI’s commitment to fostering sustainable international partnerships that promote local research leadership, build institutional capacity, and advance evidence-informed public health practices.