በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ምርምር እና ሥልጠና አጋርነት ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ Ethiopia-UK Public Health Research Partnership Conference Opens

በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ምርምር እና ሥልጠና አጋርነት ላይ ያተኮረው አገራዊ ጉባኤ ዛሬ ኅዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የለንደን የሃይጂን እና ትሮፒካል ሜዲሲን ትምህርት ቤት (LSHTM) እንዲሁም የጅማ፣ ሐዋሳ፣ መቐለ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ ተቋማት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ አጋርነት በዳጉ (Dagu) ፕሮጀክት እንደተጀመረ ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ በምርምር፣ በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ግምገማ እና በአቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሲሆን 9 የዶክተሬት (PhD) ተመረቂዎችን እና ወጣት ተመራማሪዎችን ማፍራት ችሏል።
በአሁኑ ወቅት ይህ ትብብር ከPhD ትምህርት አልፎ ወደ ድህረ-ዶክተሬት (Postdoctoral) ምርምር እና የሕዝብ ጤና መሪነት አቅም ግንባታ ደረጃ ማደጉ ተመልክቷል።
በቀጣይም ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
• የሀገር ውስጥ የምርምር መሪነትን እና የተቋማት ባለቤትነትን ማጠናከር፤
• ዘላቂነት ያለው የምርምር አቅምን ማስፋፋት፤
• የምርምር ውጤቶችን መረጃ ተኮር ለሆኑ ፖሊሲዎች እና ለጤና ሥርዓቱ እድገት ማዋል ናቸው።
የዕለቱ ውይይት ቀጣይ የትብብር መስኮችን ለመቅረጽ እና አጋርነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
Ethiopia-UK Public Health Research Partnership Conference Opens in Addis Ababa
———————————-
The Conference on Public Health Research and Training Partnerships in Ethiopia officially opened today, November 11, 2026, at the Ethiopian Skylight Hotel in Addis Ababa.
The conference brings together leaders and researchers from the Ministry of Health, the Ethiopian Public Health Institute (EPHI), the London School of Hygiene & Tropical Medicine (LSHTM), and major Ethiopian universities—including Jimma, Hawassa, Mekelle, and Gondar universities.
Delivering the opening remarks, Dr. Getachew Tollera, Acting Director General of EPHI, highlighted the strong, longstanding collaboration between Ethiopian and UK institutions, which began with the landmark Dagu project. That initiative focused on research, evaluating national initiatives such as the Optimising the Health Extension Programme in Ethiopia (OHEP), and institutional capacity building, which directly supported nine PhD graduates and early-career researchers.
Building on that foundation, the partnership has evolved into advanced postdoctoral research and leadership development, ensuring local researchers are equipped to address pressing public health priorities with evidence-based solutions.
Key priorities highlighted for future collaboration include:
• Strengthening local research leadership and institutional ownership.
• Expanding sustainable, long-term research capacity.
• Connecting local research to national policy making to strengthen Ethiopia’s health system.