የዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ-የኢንስቲትዩቱ ም/ል ዋና ዳይሬክተርና የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የአምስተኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ኮንግረስ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መልዕክት

የዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የመቶኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የአምስተኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ኮንግረስ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ መልዕክት
—————————
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መቶኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና አምስተኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ኮንግረስ ከሐምሌ 9 ቀን እስከ 11 / 2018 ዓ.ም. ድረስ በከፍተኛ ድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዮቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጤና እና ደህንነት ላለፈው መቶ ዓመታት በታማኝነት የዘለቀ አገልግሎትን በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
ለአብነት ያህልም የምርምር ውጤቶቻችን ከ175 ወደ 14,475 የጥናት ጽሑፎች አድገዋል : ከ40 በላይ የክልል የሪፈራል ላቦራቶሪዎችን መስርተን ህዝባችንን ባለበት ቦታ መድረስ ችለናል። ወደ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትነት ያደጉ 8 የክልል ላቦራቶሪዎች ተመስርተዋል። ለልዮ ልዮ ወረርሽኞች ፈጣን ምላሽ ሠጥተናል። የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ላብራቶሪ የስልጠና ፕሮግራም ባሉ መርሃ ግብሮች በመላው ሀገሪቷ የሚገኙ ከ40,000 በላይ የጤና ባለሙያዎችን ማሰልጠን ችለናል። እነዚህን አመርቂ ስራዎች ከልዮ ልዮ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑና እንዲሁም አጋራችን ከሆኑ ከአለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ለማከናወን በመቻላችን ታላቅ ደስታ ይሰማናል። በዚህ አጋጣሚ በአንድ መቶ ዓመት ጉዞአችን አብራችሁ ለነበራችሁ እና ለመላው ህብረተሰባችንን በአዘጋጅ ኮሚቴው ስም እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ ።
ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የመቶኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የአምስተኛው ዓመታዊ ሳይንሳዊ ኮንግረስ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ