የመሐመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ፋውንዴሽን ልዑካን ቡድን ኢንስቲትዩቱን ጎበኘ Mohamed Bin Zayed Foundation for Humanity Delegation Visits EPHI

የመሐመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ፋውንዴሽን ልዑካን ቡድን በሕብረተሰብ ጤና ዘርፍ በጋራ መሥራት የሚቻልባቸውን ዕድሎች ለመዳሰስ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
የመሐመድ ቢን ዛይድ የሰብአዊነት ፋውንዴሽን (#MBZFH) ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዘ ካርተር ሴንተር ተወካዮች ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ትኩረት የሚሹ ሐሩራማ በሽታዎችን (NTDs) ለማጥፋት እያከናወነች ያለውን ሥራ ለመገምገምና የላቦራቶሪ አቅምን ለመመልከት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የዘ ካርተር ሴንተር ተወካይ ዶ/ር ዘሪሁን ታደሰ እና የፋውንዴሽኑ አማካሪ ዶ/ር ማርያም አልማዝሩኢ በጋራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በተለይም የኦንኮሰርኪያሲስ በሽታን በማጥፋት፣ በጂኖሚክስ ምርምር እና በሞለኪውላር ላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ዙሪያ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱን የኦንኮሰርኪያሲስ ሞለኪውላር ላቦራቶሪ እና የተቀናጀ የጂኖሚክስና ባዮኢንፎርማቲክስ ማዕከልን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
Mohamed Bin Zayed Foundation for Humanity Delegation Visits EPHI to Explore Opportunities for Public Health Collaboration
A high-level delegation from the Mohamed Bin Zayed Foundation for Humanity (#MBZFH), accompanied by representatives of The Carter Center, visited the Ethiopian Public Health Institute (EPHI) to review Ethiopia’s progress in eliminating neglected tropical diseases (NTDs) and to assess the Institute’s laboratory capacity.
During the visit, EPHI Deputy Director General Dr. Getachew Tollera, The Carter Center Representative Dr. Zerihun Tadesse, and Foundation Advisor Dr. Mariam Almazrouei delivered remarks and held discussions on strengthening collaboration, particularly in onchocerciasis elimination, genomics research, and molecular laboratory capacity building.
Additionally, the delegation toured EPHI’s Onchocerciasis Molecular Laboratory and the Integrated Genomics and Bioinformatics Core Facility.
#EPHI #MBZFH #TheCarterCenter #NTDElimination #OnchocerciasisElimination #Genomics #PublicHealth #Ethiopia