የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ አፈጻጸምን ለመዳሰስ ብሎም የሀገሪቱ የህብረተሰብ የጤና አዋጆች የዓለም ጤና ደንቡን ከማስፈጸም አንጻር ያላቸውን አቅምና ክፍተቶችን በተመለከተ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ርፖርት ላይ ለመወያየት ያዘጋጀው የምክክር መርሀ-ግብር በዛሬው ዕለት ተካሄደ፡፡ አቶ አስቻለው አባይነህ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር በስብሰባው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የተደረገው የዳሰሳ ጥናት እና በዳሰሳ ጥናቱ ሪፖርት ላይ ለመወያየት የተዘጋጀው የዉይይት መርሀ ግብሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የዓለም የጤና ደንብ በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንድትችል በማገዙ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ይህ የምክክር ስብሰባ ያሉትን ክፍተቶች እና ተጠናክረው መቀጠል የሚገባቸውን በመለየቱ በኩል ብዙ ስራዎቸ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የምክክር ስብሰባው የሀገሪቱን የህብረተሰብ ጤና ልዩ ልዩ ስራዎች የሚረዳና የሚያግዝ የሕግ ማእቀፍ ዝግጅት ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች በቀጣይም አስፈላጊው የህግ ማእቀፍ እንዲቀረጽ ትልቅ እገዛ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡ በዕለቱ መርሀ ግብር መሰረት አቶ መልኬ ታደሰ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህግ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የተዘጋጀውን የጥናት ሠነድ አስመልክቶ ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ በተመለከተ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የተዘጋጀውን የዳሰሳ ጥናት በተመለከተ ደግሞ በአቶ ሰለሞን እምሩ እና በአቶ ደረጀ ሽመልስ አማካኝነት የጥናቱ ዳሰሳ ለመርሀ ግብሩ ተካፋዩች ቀርቦ ሠፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚህ ወርክሾፕ ላይ የሚገኘው ግብዓትም ተሰባስቦና ተደራጅቶ ዶክመንቱ ከጎለበተ በኃላ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶችና አጋር ድርጅቶችን በማሳተፍና ከስብሰባው የሚገኙ ግብአቶችን በማካተት የሀገሪቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር አዋጅ የሚወጣ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
×
- Home
- About us
- Latest News
- Research
- PHEM
- Laboratory Services
- Publications